የዓለም የኤድስ ቀን በታህሳስ 22 ቀን የሚከበር አመታዊ ሥነ ሥርዓት ነው። ይህ የዓለም አቀፍ ቀን ስለ ኤች አይ ቪ ኤድስ ግንዛቤ ለመፍጠር እና በበሽታው የሞቱትን ለመዘከር የተዘጋጀ ነው። ቀኑ ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር ለሚኖሩ ወገኖች ድጋፍ የምናሳይበት በሽታውን ለመከላከል ቁርጠኛ ለመሆን የሚያስችል አጋጣሚ ነው።
እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ዘገባ ከ1980ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ ኤድስ ከ35 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ገድሏል። እ.ኤ.አ. በ 2015 ኤድስ የ1.1 ሚሊዮን ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል። እንዲሁም በ 2017 940,000 አዲስ በኤች አይ ቪ የተያዙ እና 910,000 ከኤድስ ጋር የተዛመዱ ሞት ተመዝግቧል። ኤችአይቪ/ኤድስ አሁንም በዓለም ዙርያ ትልቅ የጤና ችግር እንደሆነ ቆይቷል። በዓለም አቀፍ ደረጃም 37.9 ሚሊዮን ሰዎች ከበሽታው ጋር ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል። ከእነዚህ ውስጥ 19.2 ሚሊዮን ያህሉ ሴቶች እና 3.2 ሚሊዮን ህጻናት ናቸው። የአቅመ ሔዋን እድሜ ላይ ለሚገኙ ሴቶች ሞት ዋነኛው መንስኤ ኤድስ ነው።
ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር በሚደረገው ትግል ትልቅ መሻሻል ቢታይም በሽታው በሰዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማሳደሩን ቀጥሏል። የዓለም የኤድስ ቀን ስለ ኤችአይቪ/ኤድስ ግንዛቤ ማስጨበጥ እና ከበሽታው ጋር ለሚኖሩ ወገኖች ድጋፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠቃሚ ማሳሰቢያ ነው።በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ኤድስን በመዋጋት ረገድ ህብረት እንዲፈጥሩ እድል የሚሰጥ አጋጣሚ ነው።
በአለም ኤድስ ቀን ለመሳተፍ ብዙ አማራጮች አሉ ለምሳሌ በዚህ ዙርያ በሚዝጋጁ ዝግጅቶች ላይ መገኘት፣ መድሀኒት ለማግኘት ለሚሰሩ ድርጅቶች በመለገስ፣ ከበሽታው ጋር የሚኖሩትን ለመርዳት ጊዜዎን በፈቃደኝነት በመስጠት ወይም በቀላሉ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ልክ እንደዚህ አይነት ጽሑፍ/ፖስት መልቀቅ ይቻላል። ስለዚህ በዚህ ርዕስ ላይ ተሳትፎ እና ግንዛቤን ለማሳደግ ሼር፣ ላይክ በማድረግ አስተያየት ይስጡ።
ለጊዜዎ እናመሰግናለን፣ እርስዎም ከኤድስ ጋር በሚደረገው ትግል ከእኛ ጋር እንደሚተባበሩ ተስፋ እናደርጋለን።