❇️ኬ ኤም ኤስ ኢ ቲ ኤች ኽልዝ ትሬዲንግ አ.ማ ጤናዎ ዲጂታል ኽለዝ (TENAWO Digital Health , www.tena-wo.com ) በማበልፀግ በአጭር የጥሪ ማዕከል ፤ በሞባይል መተግበሪያና ድህረገፅ የOnline የጤና ማማከር አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ❇️ማህበሩ አሁን ካለዉ በብይኑ መረብ ከማማከር አገልግሎት እድገቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የሚመጣ ቢሆንም በተሻለ በተጨማሪ ሌሎች ስራዎችን በመስራት የተሻለ ቁመና ላይ ለመገኘት የተለያዩ አማራጭና ተጨማሪ እቅዶች አሉት። ❇️በዚህም የተነሳ የአበላት ተሳትፎና እንቅስቃሴ ወሳኝ መሆኑን ይረዳል። ❇️እእንደሚታወቀው ማህበሩ በይፋ ለህዝብ የሼር ሽያጭ ማዉጣቱ የሚታወቅ ሲሆን ቃል ገብተዉ ክፋያ ያልጀመሩና ጀምረዉም ያላጠናቀቁ አባላት ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ የማህበሩ ቦርድ ገምግሟል። አበላትም ቃል ገብተዉ ያልጀመሩትም እንዲጀምሩ የጀመሩት ደግሞ እንዲጨርሱ በተለያዩ መንገዶች ሲገልፅ ቆይቶ የሼር ሽያጭ ጊዜዉ ተጠናቆ ተዘግቷል። ነገር ግን ሼር ለመግዛት ቃል የገባችሁና ያልጀመራችሁ እንዲሁም ጀምራችሁ የሼር ግዚዉን ያልጠናቀቃችሁ አበላት በሙሉ ክፍያችሁን በሚከተለዉ ዝርዝር ሁኔታ እንድትፈፅሙ የማህበሩ ቦርድ ያሳስባል። 1) ማህበሩ በገለፀዉ መሰረት ቃል ገብታችሁ ክፍያ ያልጀመራችሁ እንዲሁም ጀምራችሁ ያልጨረሳችሁ ለመጨረሻ የጊዜ ገደብ ከመጋቢት 4/2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2/2017 ዓ.ም ባለዉ ጊዜ ውስጥ አጠናቃችሁ የሼር ሰርቲፊኬት እንድትወስዱ ሲል የማህበሩ ቦርድ ማሳሰብ ይፈልጋል ። 2) የማህበሩ ቦርድ ቃል ገብተዉ ክፍያ ላልጀመሩና ጀምረዉ ያልጨረሱትን ዝርዝር ከላይ በተቀመጠዉ ጊዜ ገደብ መፈፀም ካልቻሉ ለዉሳኔ ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ ባስቸኳይ እንዲወሰን ያደርጋል። 3) ክፍያችሁን ያጠናቀቃችሁና ሰርቲፊኬት የወሰዳችሁም አሁን ላይ እየወሰዳችሁ ያላችሁም የማህበሩ ቦርድ እያመሰገነ ጠቅላላ ጉባኤ በአጭር ጊዜ በማህበራዊ መገናኛ መንገዶችና በጋዜጣ ስለምናሳዉቅ በትዕግሥት እንድትከታተሉ ሲል የማህበሩ ቦርድ ያሳስባል። ❇️የጤንነትዎ ዋስትና በጤናዎ !!! ግንቦት 13 /2017 ዓ.ም የኬ ኤም ኤስ ኢ ቲ ኤች ኽልዝ ትሬዲንግ አ.ማ ቦርድ አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ