የጤናዉ ዘርፍ እንደሃገር ትልቅ የአክሲዮን ማህበር ኢንሹራንስን ጨምሮ ይፈልጋል ፤ ለዚሁም ሁሉም የጤና ባለሙያዎችና ማህበረሰቡ የራሱን እድል የሚወስንበት ትልቅ አጋጣሚ ኬ ኤም ኤስ ኢቲኤች ኽልዝ ትሬዲንግ አ.ማ ከፍቷል።
ኬ ኤም ኤስ ኢቲኤች ኽልዝ ትሬዲንግ አክሲዮን ማኅበር (KMS ETH HEALTH Trading S.C) በይፋ የሼር ሽያጭ ከሰኔ 1/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ በመሸጥ ላይ ይገኛል።
አክስዮን ማህበሩ የሃገራችንን የጤና ስርዓት ከማዘመን ጀምሮ እስከ ትላልቅ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ለመክፈት እንዲሁም የህክምናና የመድኃኒት ፋብሪካዎችን በሃገራችን ለመገንባት ዕቅድ አዉጥቶ በተለይ የመጀመሪያዉ ኢላማ ማለትም ዲጂታል ኽልዝን በጤናዎ(TENAWO) የሞባይል መተግበሪያ ፤ ደህረገፅና የጥሪ ማዕከል በመክፈት በስራ ላይ ይገኛል።
የእርስዎንና የቤተሰብዎን ጤና በማንኛዉም ጊዜና ቦታ በባለቤትነት የሚያገኙበትን ዕድል ዛሬ መወሰን አለብዎት ፡፡
ኬ ኤም ኤስ ኢቲኤች ኽልዝ ትሬዲንግ አክሲዮን ማኅበር (KMS ETH HEALTH Trading S.C) ከኢትዮጵያ፣ ካናዳ፣ እንግሊዝና እና አሜሪካ በመጡ ባለሙያዎች እና የፈጠራ ባለሙያዎች የተቋቋመ በጤና አጠባበቅ ዲጅታል ዘርፍ እንዲሁም አገልገሎትና ምርት ላይ የተሠማራ በኢትዮጵያ የመጀመርያው ኩባንያ ነው። ደርጅቱ የሚሰጠው በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት በህብረተሰቡ የእለት ከእለት የህይወት እንቅስቃሴ ውስጥ ወሳኝ ሚና በመጫወት ቀላል የማይባል አስተዋጽኦ ለህብረተሰቡ ያበረክታል ፡፡በዚህም ጤናዎ( TENAWO) የሞባይል መተግበሪያ እና ድረ-ገፅ እንዲሁም የጥሪ ማዕከል በስራ ላይ አዉሎ አገልገሎት እየሰጠ ይገኛል ፡፡
በተጨማሪም በኩባንያው ስም የህክምና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ለመክፈት፤ የመድኃኒት እና የህክምና መገልገያዎችን ወደሀገር ውስጥ በማስመጣት በተመጣጣኝ ዋጋ ለማከፋፈል ፤ለመንግሥታዊ የጤና ተቋማት ዲጂታል የጤና ስርዓት መዋቅር በመዘርጋት እንደ አንድ ክንፍ ለማገልገል እንዲሁም በኢትዮጵያ የፋርማሲዩቲካል እና የህክምና መሳሪያዎች አምራች ፍብሪካዎችን ለመገንባት ዝግጅቱን ጨርሶ የጤና አግልገሎት ከሁሉም በላይ መሰረታዊ የሰው ልጅ ፍላጎት ስለሆነ ኩባንያዉ በይፋ የህዝብ መሰረትና ባለቤትነት እንዲኖረው በማሰብ ህዝባዊ የሆነና ህዝባችንን በማሳተፍ የተሻለና ቀልጣፋ የጤና ስርዓት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማሰብ ጭምር የሼር ሽያጭ የጀመረ መሆኑን በይፋ እናበስራለን ፡፡
በሃገራችን የመጀመሪያ የሆነዉን ጤናዎ( TENAWO) የሞባይል መተግበሪያ እና ድረ-ገፅ (www.tenawo.com) እንዲሁም የጥሪ ( 9456) ማዕከል ለግል ፋርማሲዎች፣ ለላቦራቶሪ አገልግሎት አቅራቢዎች፣ ለራዲዮሎጂ ምርመራ አቅራቢዎች፣ለግል የጤና ተቋማት/ክሊኒኮችና ሆስፒታሎች፣ለዶክተሮች ቀጠሮ፣የላብራቶሪ፣ዲያግኖስቲክስና የራዲዮሎጂ ተቋማት ፤የአንቡላንስ ሰጪ፣ የኦክስጅን አቅራቢ ድርጅቶችን ፤የጤና ኢንሹራንስ፣ የቤት ለቤት ህክምና ሰጪ ተቋማትን፤ ከሃገር ውጭ የላቀ ህክምናን ለሚሹ እና ሌሎችም አገልግሎት አቅራቢዎች እና አገልግሎት ፈላጊዎች ጊዜ እና ገንዘብን የሚቆጥብ የቴክኖሎጂ ግኝት ሲሆን ይህም ቴክኖሎጂ የታክሲ አገልግሎትን ጨምሮ በጂፒኤስ 500 ሜትር ራዲየስ ውስጥ የሚፈልጉትን አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያግዝ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አገልግሎቱን በ 9456 አጭር የስልክ ጥሪ ማዕከል በመታገዝ ከላይ የተገለፁትን አገልግሎቶች ማግኘት የሚቻልበት እጅግ ዘመናዊና ቀልጣፋ አስራርን በመከተል አሁን በስራ ላይ ይገኛል፡፡
ኩባንያዉ ከ ሴኔ 1/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለጥቂት ጊዜ የሚቆይ በይፋ የሼር ሽያጭ በሁሉም ባንኮች በተከፈቱ ቁጥሮች የሼር ሽያጭ ጀምሯል፡፡ ይህን እድል ቢጠቀሙ ለእርስዎና ለቤተሰብዎ ጤና ትልቅና የማይገኝ እድል መሆኑን እንገልፅለዎታለን።
የጤና ችግር የደረሰበት ሰዉ ያውቀዋል ፤ ነገር ግን ቀድሞ መንገዱን ያስተካከለ ደግሞ መፍትሔዉ እጁ ላይ ይሆናል።
ስለሆነም የዚህ ትልቅ ኩባንያ ባለቤትና ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ከታች ያለዉን መመዝገቢያ ቅፅ ዛሬዉኑ ሞልተዉ ይላኩ።
መመዝገቢያ ቅፅ
ለበለጠ መረጃ
ስልክ ቁጥር: +251116683203/04
+251116676593
+251904868788
9456
ኢሜል: KMS@tenawo.com / kmstenawo@gmail.com
ፖስታ ሳጥን ቁጥር ፡ 2178
የማህበራዊ መገናኛ መረቦች
Twitter: https://twitter.com/TenawoApp?t=GSJz4VyC1YkUfY7xror7ew&s=09
Instagram: https://www.instagram.com/tenawo_app
linkedin: https://www.linkedin.com/in/tenawo-app-957a23229
Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100075586423620
Youtube: https://www.youtube.com/channel/UC66olQjsEe7kmCoIwbVbuGg
Telegram: https://t.me/joinchat/lNz6OiDmJiJjMmM0
webiste : www.tenawo.com
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከተማ፤ ወረዳ 07፤ ጉርድ ሾላ፣ ከሰዓሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ወደ ጃክሮስ በሚወስደው መንገድ ፣ገብርኤላ ህንፃ ሶስተኛ ፎቅ ፤ቢሮ ቁጥር 302 ፡፡